Home Tech Talk TechTalk With Solomon S22 E4 – የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ተቋም ምን እየሰራ ነው? ቆይታ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር [ክፍል 1]

TechTalk With Solomon S22 E4 – የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ተቋም ምን እየሰራ ነው? ቆይታ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር [ክፍል 1]

by EthiopianSoftware

TechTalk With Solomon S22 E4 – የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ተቋም ምን እየሰራ ነው? ቆይታ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር [ክፍል 1]



አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከኛ ጋር ለመቆየት መጥቷል። ይህንን ቴክኖሎጂ አዳፕት ማድረግ እንጂ አቮይድ ማድረግ አንችልም። AI በትራንስፖርት፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በሚሊቴሪ፣ በኮንስትራችክሽን፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጤና ጥበቃ እናም በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ውስጥ ገብቶ ይሰራል። ይህ ዘርፍ ላደጉት አገራት የተተወ ቅንጡ ቴክኖሎጂ ሳይሆን፣ ታዳጊ ሃገራትም ላሉባቸው መሰረታዊ ችግሮች ማለትም በጤና አጠባበቅ፣ በእርሻ፣ በፋይናንስ እና ሌሎችም ዘርፎች ውስጥ ተተግብሮ መፍትሄ ስለሚያመጣ ትኩረት መስጠቱ ወሳኝ ነው።

ከዚሁ አኳያ ከተቋቋመ ገና ሁለት ዓመት ያህል እድሜ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ተቋም ምን ተጨባጭ እና ችግር ፈቺ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል? የጡት ካንሰር፣ የቆዳ በሽታ፣ የአዕምሮ ዕጢ ህክምናዎችን ለማገዝ፣ በግብርና አሰራሩ የእጽዋት በሽታን ቀድሞ በማወቅ የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ፣ በፋይናንሱ ዘርፍ የብድር አሰጣጥን ለማቀላጠፍ፣ ማሽኖች በNLP (Natural Language Processing) የAI ዘርፍ ቋንቋዎቻችንን ተምረው የተለያዩ ተግባራት እንዲፈጽሙና ሌሎችም በተቋሙ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ከፍተኛ አመራሮቹ ጋር ያደረኩት የመጀመሪያ ክፍል ጭውውት እነሆ

You may also like

Leave a Comment