Quantum የወደፊቱ ኮምፒውተር – ቆይታ በIBM የQuantum Education Lead ከሆነው አብርሃም አስፋው ጋር! S17
ከስልሳ ዓመታት በፊት ከነበረው አንድን ቤት ከሚያክል ግዙፍና እጅግ ቀርፋፋ፣ ነገር ግን በሚሊዮን ዶላር ከሚያስወጣ የመጀመሪያው “ENIAC” የተሰኘ ኮምፒውተር ተነስተን ዛሬ ላይ በአመርቂ ሁኔታ በሙከራ ላይ አስካለው የኳንተውም ኮምፒውተር ድረስ ያለው የዘመናዊ ኮምፒውተር ታሪክ አስገራሚ የለውጥ ጉዞን አርድጓል። ለመሆኑ ኳንተም ኮምፒውተር ምንድነው? እንዴት ይሰራል? ጥቅሙስ ምንድነው? ለምንስ ይህ አዲስ አይነት ኮምፒውተር አስገራሚ ሆነ? በእነዚህ እና ሌሎችም ርእሶች ላይ ከኔ ጋር ለመጫወት በመስኩ ከተሰማራ እንግዳ ጋር ያደረኩት ቆየታ እነሆ።
እንግዳዬ አብረሃም አሰፋ ይባላል። አብርሃም አሰፋ በአሁን ሰዓት በIBM ኩባንያ የQuantum computing team ውስጥ የquantum education lead በመሆን እያገለገለ ይገኛል። የዶክትሬት ዲግሪውን ከPrinceton University በexperimental quantum computation ሊያጠናቅቅም ሳምንታት ብቻ ይቀሩታል።