Watch TechTalk with Solomon S13 Ep2 – ቆይታ ከዶክተር እሌኒ ጋር (ክፍል አንድ)
የዛሬዋ እንግዳዬ ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን ናት። ባሁን ሰዓት blueMoon Ethiopia የተሰኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በእርሻ ተኮር የፈጠራ ግንድ ስራ ላይ የተመሰረተ ተቋም መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆና እየሰራች ይገኛል። ዶክተር እሌኒ የEthiopia Commodity Exchange (ECX) መስራችና የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናት። ወደሃገሯ ከመመለሷ በፊት በፊት በዓለም ባንክ፣ በተባበሩት መንግስታ Conference on Trade and Development in Geneva እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ አገልግላለች። ዶክተር እሌኒ፣ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከታዋቂው ኮርኔል ዩኒቨርስቲ፣ የማስተርስ ዲግሪዋን ደግሞ በእርሻ ኢኮኖሚ ከሚሺጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ፣ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪዋን በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ ከታዋቂው ስታንፈድ ተቀብላለች። የዶክትሬር ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፏ በኢትዮጵያ የጥራጥሬ ገበያ ላይ ያተኮረ የምርምር ጽሁፍ ሲሆን፣ በአሜሪካ የእርሻ ኢኮኖሚ ማህበር ምርጥ ጥናታዊ የመመረቂያ ጽሁፍ ተብሎ በ1999 ዓ.ም. ሽልማት ተበርክቶላታል።
My guest today is Dr. Eleni Zaude Gabre-Madhin, founder and chief executive officer of blueMoon Ethiopia, the first Ethiopian agribusiness incubator this coming Friday on EBS! She is the founder and former CEO of Ethiopia Commodity Exchange (ECX). Prior to that, she worked at several international organizations including the World Bank and UN’s Conference on Trade and Development. She holds a PhD in applied economics from Stanford University, MSc in Agricultural Economics from Michigan State University, and BA in economics from Cornell University, and was awarded Outstanding Dissertation by the American Agricultural Economics Association in 1999 for her research on Ethiopian grain markets.
Watch Ethiopian tech show TechTalk With Solomon. Share and comment this video.