Home Amharic Watch S7 Ep.5 – Artificial Intelligence -TechTalk With Solomon

Watch S7 Ep.5 – Artificial Intelligence -TechTalk With Solomon

by Ethiopian Software

Watch S7 Ep.5 – Artificial Intelligence -TechTalk With Solomon



This is one of my favorite topic and show! Have you ever wondered about artificial intelligence? How it started, its current advancement, and it future state?
We now have robots walking like us & taking stairs up & down; robots that can ride bike; robots with four leg, walking like animals; a robot on Mars alone doing amazing research;; robots that can do amazing surgery – all these a result of artificial intelligence.
Artificial intelligence is also among us in our everyday lives – GPS systems, Siri Voice Recognition System, driverless cars, drones, manufacturing robots, our smartphones, tablets, computers…
Will AI take over humans by replacing us in our jobs and even control us by becoming smarter than us? Enjoy & share!

ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ) አስገርሟችሁ ያውቃል? ይህ ቴክኖሎጂ ከየት እንደተነሳ፣ አሁን ምንላይ እንዳለና ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችልስ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
ልክ እንደሰው የሚራመዱና ሳይወድቁ ሚዛናቸውን ጠብቀው ደረጃ መውጣትና መውረድ የሚችሉና መሰናከልን መቋቋም የሚችሉ ሮቦቶች፣ ብስክሌት መንዳት የሚችሉ ሮቦቶች፣ ከጎን ቢገፈተሩ ወይም በሚያዳልጥ የበረዶ መሬታ ላይ እንኳን ቢሄዱ ሚዛናቸውን ጠብቀው እንደ እንስሳት መራመድ የሚችሉ ባለ አራት እግር ሮቦቶች፣ በብዙ ሚሊየን ኪሎሜትር ተጉዞና Mars ላይ ብቻውን ሄዶ አስደናቂ ምርምር እያደረገ መረጃን ለሰው ልጅ የሚያቀብል አስደናቂ ሮቦት፣ በሰው ልጅ እጅ ለማከናወን የሚያስቸግርን ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ሮቦቶች እና ሌሎችም አስደናቂ የቴክቦሎጊ ፈጠራ ውጤቶች ናቸው።
በተጨማሪም፣ በየዕለት ህይወታችን ውስጥ አርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ አብረውን አሉ – የGPS ሲስተሞች፣ እንደ Siri ያሉ የVoice Recognition ሲስተሞች፣ ያለሰው ራሳቸውን የሚነዱ መኪኖች (driverless cars)፤ ድሮኖች፣ ፍብሪካ ውስጥ ያሉ ሮቦቶች፤ ስልኮቻችን፣ ታብሌቶቻችን፣ ኮምፒውተሮቻችን…
እኛው የፈጠርናቸው ሰው ሰራሽ ክህሎት ያላቸው ማሽኖች እኛኑ ከስራ ውጪ ያደርጉን ይሆን? ከዚያም አልፎ እኛን በክህሎት አልፈው በመላቅ በቁጥጥራቸው ስር ያደርጉን ይሆን?
በዚህ ፕሮግራም ይህን አስገራሚ ቴክኖሎጂ የማስቃኝበት ፕሮግራሜ አቀርባለሁ፤ ይማሩበት፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!
Watch Ethiopian tech show TechTalk With Solomon. Share and comment this video.

You may also like

Leave a Comment