Watch S7 Ep.10 Pt.2 – Design & Technology with Industrial Designer Jomo Tariku – TechTalk with Solomon
ስነ-ጥበብና ሳይንስ | ዲዛይንና ቴክኖሎጂ Art & Science | Design & Technology
በስነ-ጥበብና በሳይንስ እንዲሁም በዲዛይንና በቴክኖሎጂ መካከል ያለውን ግንኙነት አስባችሁ ታውቃላችሁ?
ኢንደስትሪያል ዲዛይን ስለሚባልስ ሙያ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ይሄ ትምህርትና ሞያስ በኢትዮጵያ ያልተለመደው ለምንድነው?
በየዕለት ኑሯችን የተለያዩ ቁሶችን ስናይ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ምንድነው? ቴክኖሎጂ ወይስ ዲዛይን?
ከጥቃትንና ቀላል ቁሶች ከሆኑት ጥፍር መቁረጫ፣ ማብሪያ ማጥፊያ፣ የበር ቁልፍ፣ የሻይ ማፍያ ጀበና አንስቶ እጅግ ተወሳሰቡ እንደ ስልክ፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሶች፣ ኮምፒወተሮች፣ መኪናዎችና አውሮፕላኖች እና ከመሳሰሉት ነገሮች በስተጀርባ በርካታ አስደናቂ የስነ-ጥበብና የዲዛይን ባለሞያዎች እንዳሉስ ታውቃላችሁ?
በሁለት ክፍል ባቀረብኩት ዝግጅት ኢንደርስትሪያል ዲዛይነር ከሆነውና በአሁን ሰዓት በዓለም ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በዲዛይነርነት እንዲሁም ደግሞ ጆሞ ዲዛይን ፈርኒቸር የተሰኘውን የራሱን ድርጅት አቋቁሞ ለየት ያሉ የቤት እቃዎች ዲዛይን አርድጎ በመስራት ላይ ከሚገኘው ከእንግዳዬ ጆሞ ታሪኩ ጋር አብረን በዲዛይንና ቴክኖሎጂ ዙሪያ በሰፊው እንጫወታለን። ስለዲዛይንና ይኸው ሞያ በቴክኖሎጂ የፈጠራ እድገት ላይ ስላለው ተጽእኖ እንዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሮአችን ላይ በምንጠቀምባቸው ቁሶች ላይ ምን ያህል የጎላ አሻራ እንዳለው እናያለን።
Art & Science | Design & Technology
What is the connection between art & science or design & technology? Have you heard about a professional field called Industrial Design? Why is it not practiced in Ethiopia?
When you see everyday things, what comes to your mind? Technology? Or the design aspect of it? From simple mechanical nail clippers, light switches, door locks, and tea pots, to very sophisticated devices like phones, home electronics, computers, cars, planes, do you know that there are so many amazing artists and designers behind all these amazing things?
In this episode, I present to you a special guest to discuss this wonderful topic. Jomo Tariku is an industrial designer who is currently working at The World Bank as a designer. He also runs his own contemporary furniture design company called Jomo Design Furniture (JDF).
Watch Ethiopian tech show TechTalk With Solomon. Share and comment this video.
1 comment
sol..thanks…ke hulum program. .yante 1na new..ur so smart bro