Watch S11 Ep. 11 – Amazon, The Top African Architect & Other Latest Tech News – TechTalk With Solomon
የመጀመሪያው የኦንላይን ሽያጭ አንድን መጽሃፍ በ1995 ዓ.ም. በ 27.95 ዶላር በመሸጥ የጀመረው አማዞን ዛሬ በ1 ሰከንድ ብቻ እስከ 500 የግዢ ትዕዛዞችን ሲያስተናገድ፣ በመላው ዓለም ከ244 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉትና በአመት በአማካይ ወደ 130 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ እንደሚያከናውን ይነገራል። የኢንተርኔትና የኢ-ኮሜርስ ሃይል እንዲሁም ስለአማዞን ግዙፍነትና ስለመስራቹ ጄፍ ቤዞስ፤ በታዋቂው የታይምስ መጽሄት ላይ በየዓመቱ በሚወጣውና ታዋቂ ስዎች በሚሰፍሩበት “The 100 Most Influential People” በተሰኘ የ2017 ዓ.ም. መቶ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ሰለተካተተው አፍሪካዊ አርክቴክት፤ ተጣጣፊው ቤት፣ ግንበኛው ሮቦት፣ እና ሙሉ በሙሉ በ3D ህትመትና የሮቦት ብቃት ስለሚሰራው የወደፊቱ “futuristic” ቤት በዚህ ፕሮግራም ላይ የማቀርባቸው ዝግጅቶች ናቸው።
Amazon started its online business by selling the first book for $27.95 in 1995. Today the e-commerce giant sells up to 500 items per second serving its 240 million customers around the world and generating annual sales revenue of $130 billion. The power of Internet & e-commerce – Amazon & its founder Jeff Bezos; the world class African architect who made it to Time magazine’s 2017 “The 100 Most Influential People” list; the foldable house; the bricklaying robot; the futuristic house that is being fully built by 3D printing and robotic technology are the topics for this episode.
Watch Ethiopian tech show TechTalk With Solomon. Share and comment this video.